- venacava16 wrote:
- በአሁኑ ሰዓት የተሻለ ሊባል የሚችል ሪሲቨር ምንድነው ጥቅሙንና ጉዳቱን ዘርዘር አድርገህ ብታብራራልኝ
ጥያቄህ በተዛማጅ አርዕስት ዉስጥ ቢነሳ ጥሩ ነበር፡፡ ለዛሬ ቀደም ብለህ አስቀምጠህ ከነበረበት የሱፐርማክስ ቶፒክ ዉስጥ ወጦ ከላይ በምታየው
በአዲስ ቶፒክ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ ለወደፊቱ ግን አንተ እራስህ በሚቀርበው ቶፒክ ዉስጥ(ከሌለም አዲስ በመክፈት) ጥያቄዎችህን ለማኖር ሞክር፡፡
እንግዴህ እንደማንኛውም እቃ አማራጭ ስታይ ኪስህን አብሮ ማየቱ የማይቀር ነው፡፡
እዚሁ ፎረም ላይ የሪሲቨር ወቅታዊ ዋጋ የሚለው ላይ ዋጋቸውን በማየት ለመነሻ የሚሆንህን ሃሳብ መያዝ ትችላለህ፡፡
በአሁኑ ሰአት ያሉትን ሪሲቨሮች በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች ከፍየ ለማሳየት ልሞክር፡፡ በተለምዶ ገብያ ዉስጥ የሚጠሩበትን ስም ነው የተጠቀምኩት፡፡
1. SD ሪሲቨርእነዚህ ሪሲቨሮች በዋጋ በጣም ርካሾቹ ሲሆኑ በሚሰጡት አገልግሎት ግን ዉስንነት አላቸው፡፡
በአሁን ሰአት አሉ የሚባሉ ጥሩ ቻናሎች ስርጭታቸውን ወደ HD እና DVB-S2 በመውሰድ ላይ በመሆናቸው በእነዚህ ሪሲቨር
ያንን አገልግሎት ማግኘት አትችልም፡፡ ሆኖም ግን ቀደም ብለው ሪሲቨር የገዙ ሰዎች ሌሎች አማራጮች ስላልነበሯቸው በበርካታ ቤቶች ዉስጥ
አሁንም አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ ያም ማለት ያገለገሉ የዚህን አይነት ሪሲቨሮችን በቅናሽ የምታገኝበት እድሉ የሰፋ ነው፡፡
በዚህ ምድብ በብዛት የሚታወቁት የይሮስታር ሪሲቨሮች ናቸው፡፡ እነዚህ ሪሲቨሮች በአገልግሎት ቆይታቸው ጥሩ ሊባሉ የሚችሉ ዓይነት ናቸው፡፡
በርግጥ በአሁኑ ሰአት የሚገቡት የይሮስታር ሪሲቨሮች HD የሚሰሩት ሲሆኑ ከታች በሁለተኛው ምድብ ዉስጥ የምናያቸው ይሆናል፡፡
2. HD ሪሲቨርእነዚህ ሪሲቨሮች ደግሞ አዲሱን የስርጭት ስታንዳርድ የሚጠቀሙ በመሆኑ ከላይ ባለው ሪሲቨር ልታይባቸው የማትችላቸውን ቻናሎች እንድታይ
ይረዱሃል፡፡ ዋጋቸው ግን ከSD ሪሲቨር ትንሽ ጨመር ይላል፡፡ ጎንደር በረንዳን ዞር ዞር ብለህ በዚህ ሰአት እየተሸጡበት ያለውን ዋጋ መቃኘት
ትችላለህ፡፡ ከነዚህ ሪሲቨሮች አብዛኞቹ DVB-S2 ን ሰፖርት ያደርጋሉ፡፡ ሆኖም ግን አንዳንድ የማያደርጉም አሉ ስለዚህ HD ከገዛህ አይቀር
DVB-S2ንም ጭምር እንደሚሰራ ቼክ ብታደርግ ጥሩ ነው፡፡
በዚህኛው ምድብ ላይ በብዛት የሚመረጠው iBox 3030 ነው፡፡ በተለይ ሶፍትዌር አፕዴት በየግዜውስለሚለቀቅለት፡፡ ሱፐርማክስ HDም ጥሩ
ናቸው፡፡ ብዙ አይነት ሞዴል አላቸው፤ ከነዚህ ዉስጥ SM 9200 CA HD, SM 9700 ca gold plus, SM 2425HD...
ሰዎች በብዛት ከሚመርጧቸው ዉስጥ ናቸው፡፡ እዚህጋ ግን ስማቸው በጣም ተመሳሳይ ሆኖ ስራቸው ግን በጣም የተለያዩ አሉ፡፡ ለምሳሌ
የሞዴላቸው ቁጥር ተመሳሳይ ይሆንና አንዱ ሱፐርማክስ ፓወርቴክ ሲል ሌላኛው ደግሞ ፓወርፕላስ ይላል፡፡
ስለዚህ ትንሽ ጠንቀቅ ብሎ ስፔስፊኪሽናቸውን በሚገባ በማየት መለየት ያስፈልጋል፡፡ የይሮስታር HD ሪሲቨሮች በምስል ጥራታቸው ጥሩ የሚባሉ
አይነት ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ሶፍትዌር አፕዴት በቀላሉ ለማግኘት ያስቸግራል፡፡ እንግዴህ ከላይ የጠቀስኩልህ በአገራችን ገባያ በስፋት ከሚገኙት ዉስጥ
በብዛት በገዚዎች ዘንድ ተመራጭ የሆኑትን እንጂ በአጠቃላይ ከሁሉም የሪሲቨር ሞዴሎች ጋር ተወዳድሮ አለመሆኑን እንድትረዳ እፈልጋለሁ፡፡
3. ፓወርቩ ሪሲቨርእነዚህ ሪሲቨሮች ከላይ የተጠቀሱትን ሁለቱ ሪሲቨሮች የሚሰሩትን ቻናሎች ይሰራሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በፓወርቩ የተዘጉ ቻናሎችንም ይከፍታሉ፡፡
በተለይ የስፖርትና መዝናኛ ቻናሎችን ማግኘት የምትፈልግ ከሆነ እነዚህኞቹ ተመራጮች ናቸው፡፡ እዚህ ጋ ግን ልብ ማለት ያለብህ እነዚህን በፓወርቩ
የተዘጉ ቻናሎችን ለማግኘት ከፈለግህ ከሪሲቨሩ በተጨማሪ ትልቁ ሳህን እና የC ባንድ LNBም ሊኖርህ ያስፈልጋል፡፡ ያው አብዛኛው ሰው የሚጠቀመው
በትናንሾቹ ሳህኖች ስለሆነ ይህም ተጨማሪ ወጪ ሆኖ ሊወሰድ ነው እንግዲህ፡፡
የፓወር ቩ ሪሲቨሮችም የተለያዩ አይነት አሉ፡፡ ለምሳሌ አንዳንዱ እራሱ አውቶ ሮል ሲያደርግ ሌሎቹ ደግሞ አንተ እራስህ ኪ በተቀየረ ቁጥር
አዲሱን ኪ ፈልገህ ማንዋሊ ማስገባት ያለብህ አይነቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ ኮሮኔት የሚባለው አውቶ ሮል አያደርግም፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ሶፍትዌራቸው
ቶሎ የመበላሸት እና ስታክ የማድረግ ባህሪ አላቸው፡፡ እነዚህ ሶፍትዌራቸው በቀላሉ የማይገኙትን ብዙ ሰው አይመርጣቸውም፡፡ ያው እዚህም
ላይ እንግዴ ዋጋ ትልቁን ሚና ይጫወታል፡፡ በአሁኑ ሰአት ላይፍስታር እና ፍሪሳት ብዙ ቅሬታ የማይቀርብባቸው አይነቶች ናቸው፡፡ ዋጋቸውም ቅናሽ
ነው፡፡ ጂ-ስካይ ይበልጥ ተመራጭ ነው ግን ዋጋውም በተነጻጻሪ ትንሽ ጨመር ይላል፡፡ እነዚህ ከላይ የጠቀስኩልህም እንደየሞዴሎቹ ዋጋቸው የለያያል፡፡
ለምሳሌ ጂ-ስካይ ቪ6፣ ቪ7፣ቪ8 የሚባሉ ሞዴሎች አሉት፡፡
በአጠቃላይ ዋና ክፍልፋዮችን እንደዚህ ካስቀመጥን፣ ከዚ ዉጭ የተለያዩ ንኡስ ክፍልፋዮችን ፍላጎታችንን መሰረት አድርገን ልናደርግ እንችላለን፡፡
ለምሳሌ ሪሲቨሩ ፍላሽ ይቀበላል? ከፍላሽ ላይ ሙዚቃዎችን እና ፊልሞችን ያጫውታል? የHDMI አውትፑት አለው? የVGA አውትፑት አለው?
ሪከርድ ያደርጋል? ታይምሽፍት ያደርጋል? (ታይም ሽፍት ማለት እያየን ባለበት ሰአት ሌላ ጉዳይ ሲያጋጥመን አቁመን ጉዳያችንን ከጨረስን
በኋል ካቆምንበት መቀጠል የሚያስችለን ፊቸር ነው፡፡) የHD የምስል ጥራቱ እስከ ስንት ፒክስል ነው? ኦቨር-ዘ-ኤይር ትዩን ያደርጋል?
ምን ምን ኪ ይቀበላል(ቢስ ኪ ይቀበላል)? አንድ ቻናል እያሳየ ሌላ ሪከርድ ማድርግ ይችላል(ስንት LNB-in አለው)?
ዝርዝሮቹ ብዙ ቢሆኑም በአሁን ሰአት የሚገቡት ግን በአመዛኙ ባላቸው ፊቸር ተመሳሳይነት ይታይባቸዋል፡፡
እንግዴህ ከላይ ያስቀመጥኩትን ሃሳብ ከያዝክ ቀሪው ከኪስህ ጋር መማከር ነው የሚሆነው፡፡
⛔ይህን መረጃ ጠቃሚ ሆኖ ሲያገኙት በስተቀኝ በኩል የሚታየዉን ፕላስ ➕ ጫን ያርጉ፡፡