*999#ን ለመጀመሪያ ጊዜ ከሆነ የሞከሩት ባይ-ዲፎልት አማርኛ ላይ ስለሚሆን በአንዳንድ የአማርኛ ፊደላት በሌላቸው ስልኮች ወይም ሶፍትዌሮች ላይ የጽሁፍ መመሪያው አራት መአዘን ወይም ሄክሳዴሲማል ቁጥሮች ብቻ ሆኖ ሊታዮት ይችላል፡፡ ይህ ካጋጠሞት መፍትሄው ወደ እንግሊዘኛ መቀየር ነው፡፡ ከፈለጉ የሲሞ-ካርዶትን በሌላ አማርኛ ፊደላት ባሉት ስልክ ከተው ከዛም መመሪያውን እየተከተሉ ቋንቋውን ወደ እንግሊዘኛ መቀየር ይችላሉ፡፡ አለዚያም እዛው ስልክ ዉስጥ መጀመርያ *999# ን ይደዉሉና አንስውር(ሪፕላይ) ብለው ሶስት ቁጥርን ተጭነው ኦኬ ይበሉ ቀጥሎ ምላሽ ሌላ የማይነበብ ነገር ሲመጣ ደግሞ አሁንም በድጋሚ አንስወር ብለው ሁለት ቁጥርን አስገብተው ኦኬ(ሴንድ) ያድርጉ፡፡ አሁን ቋንቋው ወደ እንግሊዘኛ ስለተለወጠ እያነበቡ የፈለጉትን ፓኬጆች መግዛት ይችላሉ፡፡
ለምሳሌ ለ24 ሰአት የሚቆይ ባለ አምስት ብር ዋጋ ያለው 25ሜጋ ባይት ፓኬጅ መግዛት ፈለጉ እንበል፡-
የሚከተለውን ማድርግ ይጠበቅቦታል
*999#
እንኳን ወደ ኢትዮ ገበታ በሰላም መጡ
1.ለጥቅል አገልግሎት
2.ለተጨማሪ አገልግሎት
3.ቋንቋ ለመቀየር
የሚል ያገኛሉ እርሶም Answer ብለው 1ን አስገብተው send ይላሉ,
ለጥቅል አገልግሎት
1.ለእርሶ
2.ስጦታ ለማበርከት
የሚል ያገኛሉ እርሶም Answer ብለው 1ን አስገብተው send ይላሉ,
ለእርሶ
1.የድምጽ ጥቅል
2.የኢንተርኔት ጥቅል
የሚል ያገኛሉ እርሶም Answer ብለው 2ን አስገብተው send ይላሉ,
የኢንተርኔት ጥቅል
1.ዕለታዊ
2.ሳምንታዊ
3.ወርሃዊ
የሚል ያገኛሉ እርሶም Answer ብለው 1ን አስገብተው send ይላሉ,
ዕለታዊ
1.በ5ብር 25ሜ.ባ
2.በ10ብር 55ሜ.ባ
3.በ15ብር 100ሜ.ባ
የሚል ያገኛሉ እርሶም Answer ብለው 1ን አስገብተው send ይላሉ,
የሚገዙትን ጥቅል መርጠዋል ለማረጋገጥ 1ን ያስገቡ ለመሰረዝ ሌላ ቁጥር ይስገቡ
የሚል ያገኛሉ እርሶም Answer ብለው 1ን አስገብተው send ይላሉ,
አሁን ሂሳቦ ጥቁሉን ለመግዛት በቂ ከሆነ ተሳክቷል ይሎታል አልያም እንደሁኔታው አልተሳካም ሂሳቦን ያስተካክሉ ይሎታል፡፡ ከተሳካ ማረጋገና የአጭር የጽሁፍ መልክት sms ይደርሶታል፡፡
እንግዴህ ከላይ የገዙት ባለ 25ሜ.ባ ፓኬጅ የአንድ ቀን ነው፣ አምስት ብር ያስከፍሎታል፡፡
በ24 ሰአት ግዜ ዉስጥ ይህንን 25ሜ.ባ የመጠቀም መብት አሎት፡፡ ከ24 ሰአት በኋላ ግን ኤክስፓየር ያደርጋል፡፡
ከዛ በኋላ የሚጠቀሙት ኢንተርኔት በሜ.ጋ ባይት 35ሳንቲም ይሆናል ማለት ነው፡፡
በ24 ሰአት ዉስጥ 25ሜጋ ባይቱን ጨርሰው ተጨማሪ ከተጠቀሙም ያው ለተጨማሪው 35ሳንቲም በ ሜ.ባ ያስከፍሎታል፡፡
ይህንን መረጃ ለሌሎች ሲያካፋሉ ኢትዮዲሽን በምንጭነት መጥቀስ አይዘንጉ፡፡
⛔ይህን መረጃ ጠቃሚ ሆኖ ሲያገኙት በስተቀኝ በኩል የሚታየዉን ፕላስ ➕ ጫን ያርጉ፡፡