ተዟዟሪው ዲሽ(ሞተራይዝድ ዲሽ)
አንዳንድ ጊዜ እቤቶ ቁጭ ብለው የሳታላይቶን አቅጣጫ በሪሞት መቀየር ቢቻል ብለው አስበው አያውቁም?
መልሱ ይቻላል ነው፡፡
ይህን ማድረግ የሚያስችለን የዲሽ አይነት ሞተራይዝድ ዲሽ በመባል ይታወቃል፡፡
ከስሙ እንደምትረዱት እንደዚ አይነቱ ዲሽ እርሱን የምያዟዙርበት ሞተር ተገጥሞለታል፡፡
ከኛ የሚጠበቀው ይህ ዲሽ ሳታላይቶች ያሉበትን አርክ ተከትሎ እንዲዞር አስተካክለን መግጠም ብቻ ነው፡፡
ፓወር ከሪሲቨሩ በሚሄደው co-axial ኬብል ይደርሰዋል፡፡ ያም ማለት ሌላ የኤሌክትሪክ ሶኬት መዘርጋት አይጠበቅብንም ማለት ነው፡፡
ከዛም ከሞተሩ ደግሞ አጭር ኬብል ወደ LNBው እንውስዳለን፡፡
ዋናው ስራ ከላይ እንደተገለፀው የ ሳታላይቱን አርክ ተከትሎ እንዲዞር አድርጎ መግጠም ነው፡፡ ከዛም ሪሲቨራችን ላይ ደግሞ የያንዳንዱን
ሳታላይት ቦታና አቅጣጫ መዝግቦ ማስቀመጥ ነው፡፡ ይህንን መረጃ ሪሲቨራችን ዉስጥ ከሞላን በኋላ ከአንዱ ቻናል ወደ ሌላ ቻናል ስንላዉጥ፤
የለውጥነው ቻናል ሌላ ሳታላይት ላይ ከሆነ ዲሹ እራሱን ወደተፈለገው ሳታላይት አዙሮ ማስተላለፍ ይቀጥላል፡፡
በቃ በጣም ትጉና ፈጣን ዲሽ ሰሪ ከጎኑ ሁሌም እንዳስቀመጣችሁ ቁጠሩት፡፡
ታድያ ይህን ሞተር ለመጠቀም ሪሲቨራችን የDISEQ 1.2 ወይም DISEQ 1.3 ፕሮቶኮል እንዲኖረው ሆኖ የተሰራ መሆን ይኖርበታል፡፡
አለዚያም USALS ሊኖረው ይገባል፡፡ አሁን የሚሰሩ ሪሲቨሮች ባብዛኛው እነዚህን አካተው ነው የሚሰሩት፡፡
በነገራችን ላይ የዲሹን ስኪው አንግል ዜሮ ላይ ነው የምንተወው፤ ሞተሩ ሳህኑን በአንድ ላይ ዞር በማድረግ ነው ስኪው አንግሉን የሚያስተካክለው፡፡
ከታች ባለው ምስል የመጀመርያው ሞተሩ ለብቻው ሆኖ(ከካርቶን እንደወጣ)ሲያሳይ ቀጥሎ ያለው ደግሞ ሳህኑ ላይ ተገጥሞ ይሳያል፡፡
እስተያየቶን ከስር ያስፍሩ፡፡ መረጃው ጠቅሞኛል ካሉ ከጎን ፕላስን ጫን ይበሉ፡፡
[You must be registered and logged in to see this image.]
መረጃው ጠቃሚ ሆኖ ሲያገኙት በስተቀኝ በኩል የሚታየዉን ፕላስ ጫን ያርጉት፡፡