በመጀመሪያ ለሁሉም የዚህ ፎረም አባሎች ጥያቄዬን አንብባቹ መልስ እንድትሰጡኝ እፈልጋለው ።
የኔ ጥያቄ ሪሲቨር አለኝ ። ነገር ግን ሪሲቨሬ HD አይደለም። የድሮው Eurobox EB-9700 GOLD + SD receiver ነው ።
እናም በዚ ሪሲቨር NATGEO,MTV,E2,........... ቻናሎችን ለማየት ፈልጌ አንድ LNB ገዝቼ NILESAT ላይ EUTELSAT ቀጥዬበት ነበር ።
እንዴት ነው የቀጠልከው የምትሉ ከሆነ ከዚህ ፎረም እና FACEBOOK ላይ ከሚገኙ የዲሽ ጉሩቮች ላይ POST የተደረጉትን አንብቤ ነው ።
እናም ወደ ጥያቄዬ ስገባ EUTELSAT ስሰራ ሁሉም ቻናሎች ዝግ ናቸው ። እናም እነዚህን ዝግ የሆኑ ቻናሎች የምከፍትበት ዘዴ ለEb9700gold+ በተለቀቀ አዲስ version ሶፍትዌር UPGRADE ሲደረግ መሆኑን አንብቢያለው(እውነት ይሁን፡አይሁን ግን የማውቀው ታሪክ የለም LOL) ።
እናም ይህንን ሶፍትዌር ለማግኘት እና ሪሲቨሬን አፕግሬድ ለማረግ ያልጠየኩት FRIEND, PAGE , GOOGLE, DISH FORUM, የለም ፣ ነገር ግን ሶፍትዌሩን የሚሰጠኝ አጣሁኝ፣ ዳውንሎድ ማድረግ አቃተኝ።
እናም እስከዛሬ ሁሉም ቻናሎች ዝግ ናቸው ።
ታድያ ይሄ አያናድድም በናታቹ ?
እናም ዛሬ ደግሞ ETHIO DISH AMHARIC FORUM ላይ ከላይ እንዳነበባችሁት ንዴቴን ፖስት አርጌዋለው ።
ምናልባት ከ 2289 አባላቶች ውስጥ 1 ሰው እንኩአን የሚልክልኝ አይጠፋም ፣ በዚ ደሞ እርግጠኛ ነኝ ።
በዚ በዚ ካልተረዳዳን ታድያ ምኑ ላይ ነው ይህ ፎረም ሁሉም ሶፍትዌር አለው የሚባለው ፣ ለሁሉም ጥያቄዎች መልስ እንሰጣለን የሚባለው ምኑ ላይ ነው ?
እኔ በዚ FORUM ላይ እንዲጨመር እምፈልገው ለ Eurobox EB-9700 GOLD + receiver Digiturk (ዲጂቱርክ ) ሶፍትዌር ነው ።
መልሳችሁን እጠብቃለው. . . . . .
ሌሎቻችሁም እንደኔ የየራሳችሁን ጥያቄ ለፎረሙ ማቅረብ ትችላላቹ ።